ለ2023 የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተክርስቲያን ሪትሪት (Retreat) ለተዘጋጃችሁ ሁሉ፤
አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል፡፡ የክፍሎች ድልድል ተደርጓል፡፡ ከታች የተዘረዘሩትን በጥሞና እንድታነቧቸው እያሳሰብን፣
1)08/17/2023 ሀሙስ

•3፡00 PM – 6፡00 PM፡ Check-In (ክፍሎችን መያዝ)
•6:00 PM – 7:00 PM፡ ሰላምታና የሕብረት ጊዜ
•7፡00 PM – 9፡30 PM፡ የፀሎት / የዝማሬ / የትምህርት ጊዜ

2)ለሪትሪቱ (Retreat) የሚያስፈልጉ ነገሮች፡
•መዋኘት ለምትፈልጉ (በተለይ ለልጆች) - Swimming Suits
•ከ4 ቤተሰብ በላይ ላላችሁ (በተለይ ለልጆች) Sleeping bag ወይም አነስተኛ በአየር የሚሞላ ፍራሽ (air inflatable mattress) መያዝ አስፍላጊ ነው
•ሪትሪት ሴንተሩ አንሶላዎችን፣ ብርድልብሶን፣ ትራሶችን፤ ፎጣዎችን፣ ሳሙናዎችንና ሌሎችንም ያሟላል፡፡ ምርጫችሁ ከሆነ ግን የራሳችሁን ፎጣዎችና ሳሙናዎች መያዝ ትችላላችሁ፡፡

3)ሀሙስ ማታ እራት በሪትሪቱ ቦታ አይኖርም፣ ነገር ግን በመዋጮ መልክ (potluck) ወይንም በግል ምግብን ወደ ሪትሪቱ ቦታ ይዞ በመሄድ በውጭም ሆነ በሌሎች ሥፍራዎች መመገብ ይቻላል፡፡ በዋናው መመገቢያ አዳራሽ ግን መጠቀም አይፈቀድልንም፡፡

4)ያልተመዘገባችሁትን በሪትሪቱ ቦታ ለማስተናገድ አንችልም፣ ክፍሎች ሁሉ ተይዘዋል፡፡ ዝርዝሩም ለሪትሪት ሴንተሩ ተላልፏል፡፡

5)የአየሩን ሁኔታ ያገናዘበ ልብስን መያዝ አትዘንጉ፤ አንዳንድ የእስፖርት እንቅስቃሴዎችን ለማድርግም ሆነ ጨዋታዎች ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ ትጥቅ ብትይዙ መልካም ነው፡፡

6)ልጆች በቤት ላቸውን በመዝናኛ ሰዓት የሚጫወቱበትን እንደ እግር ኳስ፣ መረብ ኳስና ቅርጫት ኳስ የመሳሰሉትን ይዘው እንዲሄዱ አበረታቷቸው፡፡

7)ስለ ቅዳሜ Ckeck-Out (ክፍሎችን ስለመልቀቅ) ዐርብ ማታ መመሪያ ይሰጣል፡፡

8)የሪትሪት አድራሻ (Heartwood Resort Conference Center)  

            N10884 Hoinville Road
           Trego, WI 54888
           Phone: 715-319-3064