የአምሥት የጾምና ፀሎት ጊዜ ለኢትዮጵያና ለቤተ ክርስቲያን

 

(ከሰኞ April 19 እስከ April 23, 2021 )

 

 Time Conference Number Conference ID 

7:00am - 8:30am

7:00pm - 8:30pm

1-848-220-3300

 1156173

 

 Prayer April19 23 2

የአምሥት የጾምና ፀሎት ጊዜ ለኢትዮጵያና ለቤተ ክርስቲያን

(ከሰኞ April 19 እስከ April 23, 2021 )

ዓላማው፡ በወቅታዊ የአገራችን ሁኔታ ላይ የእግዚአብሔርን ፊት ለመፈለግ

 

1. ሰኞ April 19/2021 በንስሃ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግ ሲሆን

1.1. ያለፈው ትውልድ እግዚአብሔርንና ሀገሩን በበደለበት ጉዳይ ምህረትን መጠየቅ 1.2. ዛሬ በሕይወት ያለነው እግዚአብሔርንና ሀገራችንን በበደልንበት ምህረትን መጠየቅ 1.3. የጌታ መንፈስ በሚያሣስበን ጉዳይ ሁሉ ንስሃ እየገቡና እያመሰገኑ መፀለይ (የሚነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ 2ኛ ዜና 7፡14)

 

2. ማክሰኞ April 20/ 2021: የሠይጣንን ሥራ እያፈረሱ መፀለይ ሲሆን

2.1. በቀደመው ትውልድ እየሰራ ያለውን የሠይጣንን ሥራ ማፍረስ

2.2. በዛሬው ትውልድ እየሰራ ያለውን የሠይጣንን ሥራ ማፍረስ

2.3. የእግዚአብሔር መንፈስ በሚያሳስበን ነገር ሁሉ የጠላትን ሥራ እያፈረሱና ጌታን እያመሰገኑ መፀለይ(የሚነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ ኤፌ 6፡ 10 - 18)

 

3. ዕሮብ April,21/2021 የእግዚአብሔር መልካሚቱ እጅ በኢትዮጵያ ላይ እንድትመጣ መፀለይ ሲሆን

3.1. በቀደመው ትውልድ የነበረውን ማንኛውንም መልካም ነገር የዛሬው ትውልድ እንዲያስቀጥል የእግዚአብሔርእጅ እንዲረዳን

3.2. በዛሬው ትውልድ ላይ የእግዚአብሔር እጅ በኃል እንዲመጣ መፀለይ 3.3. የእግዚአብሔር መንፈስ በሚያሳስበን ነገር ሁሉ እግዚአብሔርን እያመሰገንን መፀለይ (የሚነበበው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ፡ 1ኛ ዜና 4፡ 9 – 18)

 

4.  ሐሙስ April 22/2021 በኮሺድ ምክንያት ቤተ ክርስቲያን መሰብሰብ ባለመቻላችን የሰዎች ሕይወት እየተዳከመ እንዳይሄድ እንጸልያለን፤ በተጨማሪም ወጣቶች በዚህ ጊዜ ትምህርት ቤት ስለማይሄዱና ከጓደኞቻቸዉ ስለተለያዩ በዚህ አጋጣሚ ጠላት እንዳያገኛቸዉ እንጸልይ፤

 

5. አርብ April 23/2021 “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነዉ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል፤ የምንለምነዉንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናዉቅ ከእርሱ የለመነዉን ልመና እንደ ተቀበልን እናዉቃለን” 1ኛ ዮሐ. 5፤14_15

ይሄ ቀን ላለፉት አራት ቀናት የጸለይነዉን ጸሎት እንደተሰማን አምነን የምናመሰግንበት ቀን ነዉ፤